ጋን ኢትዮጵያ ውስጥ ለውሃ መያዣ ለጠላ መጥመቂያ እንዲሁም ለጠጅ መጣያ የሚያገለግል ከሸክላ የሚሰራ አንገት ያለው ከስሩ ክብ የሆነ፣ ባብዛኛው ጠቆር ያለ መልክ ያለው እቃ ነው። በይዘቱ ከገንቦ ሆነ ከእንስራ ይተልቃል።